ታህሳስ 18/201 5ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለማሳካት የሚያግዙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ኢንስቲትዩቱን በስልጠና፣ በማማከርና በጥናትና ምርምር የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እንዲያግዝ የተፈቀደ “East Africa Skills Transformation for Regional Integration Project”(EASTRIP) በመባል የሚታወቅ የዓለም ባንክ ፕሮጀክት ነው።

ይህ ፕሮጀክት በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ትስስር የሚፈጥር ሲሆን የስርዓተ ሥልጠና ዝግጅት፣ የአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ልምድ ልውውጥ፣ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች፣ የተለያዩ ግንባታዎችና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል 12.6 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል።
ፕሮጀክቱን ውጤታማ ለማድረግ የማማከር ሥራ የሚሰራውና ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት ቴክኒካል አማካሪ ቦርዱ ስለፕሮጀክቱ ምንነት፣ የቦርዱ ሃላፊነትና የሥራ ሂደት ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥና የትውውቅ መርሃ ግብር አካሂዷል።
የቦርዱ አባላት የተጣለባቸው ሃላፊነት ትልቅ በመሆኑና የዓለም ባንክ ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ለዘርፉ ባላቸው እውቀት፣ ልምድና ቅርበት የተመረጡ በመሆናቸው ለፕሮጀክቱ ስኬት የበኩላቸውን እንዲወጡና ለዚህም በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልፀዋል።
በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ካለው የረጅም እድሜና ልምድ አንፃር በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉ እንደሚቆጫቸውና አሁን መንግስት የሰጠው ትኩረት ያስደሰታቸው መሆኑን የተጣለባቸውንም ሃላፊነት በሙሉ ፈቃደኝነትና ቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
1. አቶ መልካሙ መኮንን የሃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተር የቴክኒካል ኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርዱ ሰብሳቢ
2. አቶ ፍስሃ ሲሳይ የሼፍ አሶሴሽን አባል
3. ወ/ሮ ሳምራዊት ሞገስ የትራቭል ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
4. ዶ/ር ሙሉጌታ አስራዕየ የሙካ ቱር ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
5. አቶ በላቸው አድማሱ የሸራተን አዲስ ሆቴል ትሬኒንግ ማናጀር አባላት በመሆን የተመረጡ ሲሆን ከመንግስት በኩል አራት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችን አባል በማድረግ የትውውቅ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።