ጥቅምት 04/2012 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 12ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው እለት ኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ አከበረ፡፡
በበዓሉ አካባበር ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ፣ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ መሪ ቃሎች ሲከበር የቆየ ሲሆን፤ በዚህ ዓመትም “ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡