የምግብ ቱሪዝምን ምን ያህል ተጠቅመንበታል?

ሰዎች የአንድን ሀገርና አካባቢ የምግብ ጣዕም ለመቅመስና ለማጣጣም የሚያደርጉት ጉዞ የምግብ ቱሪዝም ይሰኛል፡፡ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው ሰዎች ለማንኛውም አይነት የቱሪዝም ተግባራት ከሚያወጡት አጠቃላይ ወጪ 15 በመቶ ያህሉ በምግብና መጠጥ ላይ የሚውል ነው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሰፊ ባህልና የምግብ አሰራር ባለባቸው ሀገራት ደግሞ የምግብ ቱሪዝምን ለማስፋፋት የሚያስችል ዕምቅ ሀብት አለ፤ ይሁንና ይህንን የቱሪዝም ዘርፍ ምን ያክል ጥቅም ላይ ውሏል ተብሎ ሲጠየቅ መልሱ እምብዛም ነው የሚሉ ምሁራን በርካታ ናቸው።
የሆቴል ማኔጅመንት ኢንስትራክተርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሀብቱ ተካ እንደሚሉት፤ የምግብ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት ዕምቅ ሀብት ነው፡፡
የምግብ ቱሪዝም በየዓመቱ ከሰባት እስከ 12 በመቶ እድገት እያሳየ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ያለ የቱሪዝም…