ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ለሚገኙ 100 ለሚሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮች የአፍጥር ፕሮግራም ማሰልጠኛ በሆነው የገነት ሆቴል አዘጋጀ።
በዝግጅቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮችና የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የመስጠት ተልእኮ ያለው በመሆኑ የወረዳውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉና በተቋሙና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ጠንካራ ግንኙነት የሚፈጥሩ ልዩ ልዩ ሥራዎችን እንሰራለን በማለት በዛሬው ዕለት የተዘጋጀው የአፍጥር መርሃግብር የአብሮነታችን መገለጫ ነው ብለዋል። በመጨረሻም እንኳን ለ1444ኛ ዓመተ ሂጅራ የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ በማለት የአፍጥሩን መርሃ ግብር አብረው አሳልፈዋል። እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል !!
Recent Comments