የመልካ ቁንጡሬ ባልጩት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡
ቱ.ማ.ኢ ሀምሌ 19/2016 ዓ.ም

በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጩት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቋሚ የሚዳሰሱ ቅርሶች 12ኛው የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ሥፍራውን በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ካበቁት መስፈርቶች መስፈርት 3 (criterion III) ከ2.5 ሚሊየን ዓመት እስከ መጨረሻው የድንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መገልገያዎች ይዞ የሚገኝ በመሆኑ፡፡
መስፈርት 4 (criterion Iv) እስከ 2.5 ሚሊየን ዓመት እድሜ ያላቸው የተለያዩ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካሎች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ መስፈርት 5 (criterion v) የሰው ልጅ ከድንጋይ የተለያዩ መገልገያዎችን/መሳሪያዎችን ይሰራ እንደ ነበር የሚያሳዩ ስምንት የባልጩትና ሌሎች የድንጋይ መሳሪያ ማምረቻ ሥፍራዎችን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡
መልካ ቁንጡሬ ባልጩት ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጂራ በሚወስደው ጎዳና 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኝ ስፍራ ነው፡፡
የመረጃው ምንጭ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን
ትክክለኛ የተቋሙን መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/