ቱ.ማ.ኢ ጳጉሜ 05/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም የስልጠና መስኮች በትብብር ስልጠና አብረው ሲሰሩ ለነበሩ በሆቴልና ቱሪዝም የሥራ መስኮች ለተሰማሩ ድርጅቶች ምስጋና እና እውቅና ሰጠ፡፡
በመርሐ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስካሁን ከተቋሙ ጋራ ስትሰሩ ለነበራችሁ ድርጅቶች ሁሉ እያመሰገንን በቀጣይነትም ዘርፉ የማይቋረጥና ተከታታይ የሥራ ላይ ስልጠና የሚፈልግ በመሆኑ በራችሁን ክፍት በማድረግ ሰልጣኞች በቂ እውቀት እንዲያገኙ በማድረግ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻል የጋራ የቤት ሥራችን በመሆኑ አብረን እንድንተጋ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው በትብብር ስልጠና ሰልጣኞችን በፈቃደኝነት በመቀበል፣ በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ፣ ለአሰልጣኞች የሥራ ላይ ስልጠና በመስጠት ለነበሩ ሁሉም ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከድርጅቶቹ መካከል መካከል ሰልጣኞችን በፈቃደኝነት በመቀበልና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ላደረጉ እንዲሁም ሁሉም ሰልጣኞች በተመደቡበት የሙያ መስክ አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል ላደረጉ፣ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ለሸራተን አዲስ ሆቴል፣ ለሀያት ሬጀንሲ እና ሂልተን አዲስ ሆቴል የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
Recent Comments