ሪፎርሙ አገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ የሚያደርግና በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ሲቪል ሰርቫንቱ ሚናውን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ሪፎርም ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት፣ መንግስት የሚሰጠውን አገልግሎት ከብልሹ አሰራር የፀዳ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው።
በዚህም ነፃና ገለልተኛ ተቋማት ለመገንባት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ተቋማት አሰራራቸውን በማዘመን ቀልጣፋና ውጤታ አገልግሎት እንዲሰጡ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ሪፎርም ተቀርፆ ለትግበራ ዝግጁ ተደርጓል።
ለትግበራ ዝግጁ የተደረገው ሪፎርም አገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ የሚያደርግና በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ሲቪል ሰርቫንቱ ሚናውን እንዲወጣ የሚያስችል ነው ብለዋል።
በመድረኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ሪፎርም ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official