ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ህዳር 11/2013 ዓ.ም ለሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ለአጠቃላይና ደጋፊ ትምህርት ዘርፍ እየተሰጠ ያለው መሰረታዊ የሆቴልና ቱሪዝም ስልጠና ሁሉን አቀፍ እውቀትን የሚሰጥና ለስልጠና ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው መምራን ገለጹ።
የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ኪዳኔ ገረሱ ለአጠቃላይና ደጋፊ ትምህርት መምህራን በቱሪዝም መስክ መሰረታዊ የሆነ ዕውቀት ማስጨበጥ የሚችል እና ጠቅለል ያለ መረጃ እንዲኖራቸው የሚያግዝ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንን ገልጸዋል፡፡
የአጠቃላይና ደጋፊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታከለ ኛሜ በበኩላቸው ስልጠናው መሰረታዊ እውቀትን የሚያስጨብጥና መምህራን ባላቸው የሙያ መስክ እርስ በራሳቸው የሚማማሩት ትምህርት ለስልጠና ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
መምህርት እታፈራው ሲሳይም ከስራ ባልደረቦቻቸው ያገኙት ስልጠና ኢንዱስትሪውን የሚመጥን ስልጠና ለመስጠት እንደሚያስችላቸው ገልፀው ይህ መሰሉ መድረክ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩ የአጠቃላይና ደጋፊ ትምህርት ክፍል መምህራን በክፍል ውስጥ በንድፈ ሃሳብ የቀሰሙትን ትምህርት በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከልና እንጦጦ ፓርክ በመስክ ጉብኝት ያዳበሩት ሲሆን ስልጠናው ለአስር ቀናት ቆይታ ይኖረዋል፡፡