ቱ ማ ኢ ህዳር 30/2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጀ ለ18ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የሙስና ቀን በተቋማችን ተከበረ፡፡

የተቋማችን የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አቶ ታምራት ተፈራ እንደገለጸው በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ ሙስና ቀን ቢከበርም የሚፈለገው ለውጥ አላመጣም፤ ሆኖም ዘንድሮ በስነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ በሚል በስፋት እየተከበረ እንደሆነና ይህንን በአመራር የተጀመረው ለውጥ ወደ ሁሉም እንዲደርስ ርብርብ በማድረግ ሙስናን መቀነስ እንደሚቻል ተናግሯል፡፡
በውይይቱ የተገኙት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት እንደተናገሩት በሀገራችን የጥቅም ግጭትን ለመከላከል በቅድሚያ ሙስናን መፀየፍ አለብን ብለዋል፡፡ ይህም የሀገራችንን እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚፈለገው ለውጥ እንዳናሳይና በተለያዩ ጥቅሞች እንዲንጋጭ ምክንያት ሆኗል፡፡ ስለሆነም በስነ-ምግባር የታነፀ ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ በመፍጠር ሙስና ከመፈጠሩ በፊት በመከላከል ላይ በማተኮር ለሀገር ለውጥ መታገል እንዳለብን አሳስበዋል፡፡