ጥቅምት ቱ ማ ኢ ኢንስቲትዩት አብሮ ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ የሆነው ሂልተን ሆቴል ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸውን ባለሙያዎች በማምጣት ለኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች ልምድ እንዲያካፍሉ አድርጓል።ከሆቴሉ ልምዳቸውን ለማካፈል የተገኙት ሚስተር ካን አሊ የሂልተን ሆቴል ማናጀር ፣ ሚስተር ሰፌዲን ባዲ ኮሜርሻል ማናጀር እና ሌሎችም የቡድኑ አባላት በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ወደ ሥራ ሲገባ ሊያጋጥም የሚችል ተግዳሮትን እና በልምድ የሚገኘውን እውቀት ፣ በተግባር የኖሩትን ህይወት ጭምር ለሰልጣኞች አጋርተዋል።

ሰልጣኞችም ባገኙት መረጃ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ተሞክሯቸውን ላካፈሉ የሆቴል ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዝግጅቱን የጋይዳናንስና ካውንስሊንግ ማስተባበሪያ ክፍል መርቶታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et