መጋቢት 7/2015ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአገራችን ለ47ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ “Digit ALL: Innovation and technology for gender equality.” ”ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ለጾታ እኩልነት” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ደግሞ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዓሉን አስመልክቶ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በእኩልነትና ፍትሃዊነት በሁሉም መስክ ምቹ መደላድል መፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ በዓሉ ለሴቶች ብቻ የተተወ ሳይሆን ወንዶችም በጋራ የምናከብረው በዓላችን ነው ብለዋል፡፡
ሴቶች የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚ ተሳትፏቸው እንዲያድግ ያለባቸውን ጫና በመቀነስ የትምህርት ዕድሎችን ማመቻቸት ለሴቶቹ ተብሎ ሳይሆን ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ወልዴ ደፋር በዓሉን በተመለከተ ሰነድ አቅርበዋል፡፡ የሴቶችን ብርታት በፈተና ውስጥ አልፎ ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ደግሞ የህይወት ልምዳቸውን የተቋሙ አንጋፋ አሰልጣኝ ዙሪያሽ ወርቅ በላይ አካፍለዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ የሚቀርጻቸውን መሪ ሃሳቦች መሰረት በማድረግ እንደየ ሀገራቱ ተጨባጭ ሁኔታ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
Recent Comments