ሆ.ቱ.ማ.ኢ መስከረም 02/2012 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቱሪዝም ክፍል መምህራን ለአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዝዋይ ሀይቅ ላይ ጉብኝት አደረጉ፡፡
የመስክ ስልጠናው አስተባባሪና የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ኪዳኔ ገረሱ እንደገለጹት ጉብኝቱ በዝዋይ ሀይቅ ላይ የተለያዩ የአዕዋፋት ዝሪያዎችና ሎሎችም ለቱሪስት መስህቦች የሚገኙ በመሆኑ መምህራኑ በአካባቢው ላይ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማጥናት በቀጣይ ለሰልጣኞች በቂ ስልጠና ለመስጠት እንደሚያግዝ ገልጸው በአካባቢው በአስጎብኝዎች ዘንድ የሚታየውን የአቅም ክፍተት በመለየት ለቀጣይ ስራ የቤት ስራ ለመውሰድም ያግዛል ብለዋል፡፡ በሀይቁ ላይ በርካታ የቱሪስት መስህቦች መኖሩንን የበለጠ መተዋወቅ እንዳለባቸው ኃላፍዉ አክሎ ተናግረዋል፡፡
የዝዋይ ሀይቅ አምስት ደሴቶች ያለዉ ስሆን ስማቸውም ቱሉጉዶ፣ገሊላ፣ደብረሲና፣ጸደቻ፣ፉንዱሮ የሚባሉ አምስት ደሴቶች ያሉት ሲሆን ስፋቱ 434 km2፣ርዝመቱ 20 ኪሎሜትር፣ጥልቀቱ እንደሚገኝ የቱሪስት አስጎብኝው ደሴ በሪሶ ገልጸዋል፡፡
ሀይቁ ውስጥ 13 የአዕዋፍ ዝርያዎች፣አራት የአሳ አይነቶችና ጉማሬዎች ይገኛሉ፡፡ ከደሴቶ መካከል ቱሉ ጉዶ በሚባለው ደሴት ላይ በ9ኛው መቶ ክፍለዘመን ሙሴ ጽላት ለ40 ዓመታት የቆየበት ቤተክርስትያንም ይገኛል፡፡
በብሩክ ታደሰ