ለሥራና ክህሎት ሚንስቴር ተጠሪ ተቋማት ከሆኑት አንዱ በሆነው የቱሪዝም ኢንስቲትዩት በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 478 ሰልጣኞችን አስመርቀናል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉ በሀገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና ካላቸው ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛው ቢሆንም በሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ዘርፉ ለረዥም ጊዜ እየተፈተነ ቆይቷል፡፡ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት የቱሪዝም ዘርፉ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ እየተነቃቃ ይገኛል፡፡
በዚህ ወሳኝ ወቅት መመረቃችሁ የዘርፉን የሰው ሀይል ጉድለት ከመሙላት፣ ዘርፉን በማዘመን የአገልግሎት ጥራትን እና የመስተንግዶ ቅልጥፍናን ከማሻሻል ባሻገር የኢትዮጵያ ገጾች ጭምር በመሆናችሁ ኃላፊነታችሁ ከፍ ያለ ነው፡፡
የዚህ ዓመት ተመራቂዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና መላው የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ! እያልኩ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም አውጥቶ ለመጠቀም በሚደረገው ርብርብ ሁሉም ሚናውን እንዲወጣ አደራ እላለሁ !
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
Recent Comments