በዚህ መድረክ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ቦርድ ሰቢሳቢ በቁልፍ መልዕክታቸው የዘላቂ ልማት ግብን ከቱሪዝም አንፃር አንስተው ቱሪዝም ከኢኮኖሚ ዘርፍ አንዱ መሆኑን፣ከሆቴል ማህበራት፣ ከትምህርት ተቋማት፣ከማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የቱሪዝም ትስስር ማድረግ ከነዚህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ የምርምር ጽሑፎች ይጠበቃል ብለዋል።
ዶ/ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የቱሪዝም መስህብ የማይሆን ምንም ነገር የለም ። ከኛ የሚጠበቀው የዘርፉ ሙሁራንን በመጠቀም በጥናት የተደገፈ ሥራ በስፋት ማስተዋወቅ እና ማልማት ነው ብለዋል።

Recent Comments