ሰራተኞችና አመራሮች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወንጪ ሀይቅ አካባቢ ኢትዮጵያን የማልበስ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አከናውኗል።
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ /ሮ ቡዜና አልከድር ሚኒስቴር መ/ቤቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲለሙ ኃላፊነት ወስዶ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ችግኞችን እየተከለ መሆኑን የገለጹ ሲሆን መዳረሻዎችን መንከባከብ ለአከባቢው ወጣቶች ለስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በበኩላቸው የቱሪስት መዳረሻዎችን ችግኝ መትከልና እንክብካቤ ማድረግ የማሰልጠኛ ማዕከሉ ለሚያከናውኗቸው የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
በወንጪ ሀይቅ አካባቢ የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክሏል። በቀጣይነትም ከአምስት ሺህ ችግኞች በላይ በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎች ለመትከል ዕቅድ መያዙ ተገልጿል።
Recent Comments