የሊቼ ስምምነት በተፈረመበት ታሪካዊ ቦታ ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፋ።
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰራተኞች በደብረ ብርሃን ከተማ አካባቢ በሚገኘው በ1870 ዓ.ም አፄ ምኒልክ እና አፄ ዮሐንስ የሰላም ስምምነት ባደረጉበት ልቼ ላይ በሀገራዊ ኢትዮጵያን እናልብሳት መርሃግብር አምስት ሺህ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል።
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ አክሊለ ጌታቸው ለማዕከሉ ሰራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የአካባቢውን ታሪክ ገለጻ አድርገዋል።
የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚያከናውነው የችግኝ ተከላ መርሃግብር የቱሪስት መዳረሻዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ተቋሙ ለሚያከናውናቸው የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ስራዎች አስፈላጊ ናቸው።
ችግኝ የሚተከልባቸው በየመዳረሻው የሚገኙት ማህበረሰብ ተንከባክበው እንዲያጸድቁት መግባባት የተደረሰበት ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፋት ሰራተኞችም ለአረንጓዴ አሻራ የበኩላቸውን በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት በወንጪ ሀይቅ አካባቢ ከሁለት ሺህ አራት መቶ ችግኝ በላይ መተከሉ ይታወሳል።
በቀጣይም በሌሎች መዳረሻ አካባቢዎች የሚከናወን ይሆናል።