ባለድሻ አካላትና የባህልና ቱሪዝምሚስቴር ተወካዮች፣ የባህዳርና ደብረማርቆስ ዩንቨርሲቲ በምዕራቡ ጎጃም ደምበጫ በሙሉ የማህበረሰብ ኢኮሎጅ ተገኝተው ህብረተሰቡ አካባቢውን እያለማ የኢኮ ቱሪዝም ተጠቃሚ የሆነበትን ስፍራ ጎበኙ።

ተቋሙ ካለው የምርምር፣የማሰልጠንና፣የማማከር ተልዕኮ ባሻገር በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ሙያዊ ስልጠና ይሰጣል።
ሙሉ ኢኮ ሎጅ በዓይነቱ የተለየ በየትኛውም ሁኔታ ተፈጥሮን ማዕከል አድርጎ የተሰራ እና አገር በቀል እውቀትንና የማህበረሰቡን ወግና ባህል ሌሎች ለማስተዋወቅ እና ተጠቃሚ መሆንን ታሳቢ ያደረገ ነው።
የዚህ ሃሳብ ጠንሳሽና ልምድና ዕውቀቱን ለተወለደበት ማህበረሰብ በማካፈል ህዝቡ ተጠቃሚ ኦንዲሆን ያደረገው ወጣት አብይ ዓለም ኑሮውን በጀርመን አገር ባደረገበት ጊዜ ከቀሰመው ልምድ በመነሳት እንዲህ እንደሰራው ይገልፃል።
ተቋሙ በዚህ ሥፍራ ይህን የባለድርሻ አካላት ውይይት ሁሉም ቦታው ላይ ያለውን ተሞክሮ በመጎብኘት በሌሎች አካባቢዎች እንዴት ማስፋት ይቻላል የሚለውን ለመነጋገርና ሁሉም የድርሻውን እንዲወስድ ለማድረግታቅዶ ነው።
ይህን ውይይት የተካፈሉ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ
ኃላፊዎችና ተወካዮች ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን እና ይህ ሞዴል ስራ መስፋት እንዳለበት ገልጸዋል።