ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ መጋቢት 11/2013 ዓ.ም
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የ6ወር ሥራ አፈጻጸምና የባለድርሻ አካላት ወይይት መድረክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊዎች ከዘርፉ ጋር የሚሰሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ መክፈቻ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት እንደገለጹት ተቋሙ በ6ወር ያከናወናቸውን ሥራዎች ለማስቀጠልና ሌሎች የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ከባለድርሻ አካላትና ተቋሙን በቅርበት ከሚከታተለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በየጊዜው ተቋሙ የሚያከናውናቸውን ተግባራት መገምገሙ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሰልጣኞች ለማፍራት የሚያግዝ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አስቴር የውይይት መድረኩ በተለይም የተቋሙን ደምብ ለማሻሻል ለሚደረገው ጥረት በዚህ መድረክ የተገኛችሁ የስራ ኃላፊዎች የምትሰጡት ሃሳብ በጣም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የተቋሙን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በዝርዝር ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
ከቀረበው የ6 ወር የአፈጻጸም ሪፖርት በመነሳት ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት የ6ወር አፈጻጸሙ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዘርፉን በጎዳበት ወቅት ቢሆንም ተቋሙ እንደ አገር የሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ከመዘጋት የታደገ መሆኑንና በርካታ ስራዎች የተሰሩ መሆናቸውን እንደተረዱ ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ደምብ ማሻሸያና ከመዋቅር ጋር የሚነሱ ችግሮች እንዲፈቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የቋሚ ኮሚቴ አባላት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ እና ወደ ሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱም ቃል ገብተዋል፡፡
በሁለተኛው ምዕራፍ የትብብር ስልጠና ማዕቀፍ ሰነድ በተቋሙ አስተዳደርና ልማት ዲን አቶ ዳንኤል በቀለ ለውይይት ቀርቦ የማዳበሪያ ሃሳብ ከተሳታፊዎች ተሰጥቶበታል፡፡