ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ነሐሴ 03/2011 ዓ.ም በሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ የሚገኙ የሥራ ክፍሎች፣ ኃላፊዎችና የተቋሙ የበላይ አመራሮች በተገኙበት በበጀት አመቱ ዕቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት የተቋሙ ዕቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳሬክተር አቶ ሀይሉ ነገዎ በበጀት ዓመቱ የስልጠና ጥራትና ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የጥናትና ምርምር እና የምክር አገልግሎቶችን የማስፋት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ሰፊ ስራዎችን መሰራት ሰለተቋሙና ተቋሙ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃዎችን በሰፊው ተደራሽ ማድረግ እና ምቹ የሥራ አከባቢን መፍጠር በዋናነት የተያዙ ዕቅዶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አቶ ገዛኸኝ አባተ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የተቋሙ ዕቅድ ወቅታዊና የተያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ሁሉም የሥራ ክፍል የራሱን ተግባርና ኃላፊነት መወጣት እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
የኢንቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አሰቴር ዳዊት እንደገለጹት እነዚህ የታቀዱ ስራዎች ከዳር ለማድረስ ከሀገራዊ ዕቅድ አንጻር ታይቶ መዘጋጀቱ ዕቅዱን የተሻለ ያደርገዋል ፡፡
ሁሉም ሰራተኞች ለዕቅዱ ስኬት አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ርብርብ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ምቹ የሥራ አከባቢን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የገነት ሆቴል የተቋሙ አካል በመሆኑ ሆቴሉ ያዘጋጃቸው ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያሰፈልግ ወ/ሮ አስቴር ተናግረዋል፡፡
Recent Comments