የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና የካናዳው ኮለጅ ኦፍሮኪስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ውይይት አደረጉ፡፡

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና የካናዳው ኮለጅ ኦፍሮኪስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሁለተ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡
ተቋማቱ ለሰልጣኞችና የሰራተኞቻቸው የልምድ ልውውጥና የስልጠና ጥራትን ማስጠበቅ የሚቻልበት ጉዳዮች በዝርዝር ውይይት መደረጉን የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተወካይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግሩም ግርማ ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት አብሮ ለመስራት በጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡