ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ መስከረም 30/2012 ዕቅዱን አስመልክቶ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የዘንድሮን ዕቅድ ከሌላው ለየት የሚያደርገው በ2011 ዓ.ም የነበሩትን ክፍተቶች በማሟላት የተማሪ የቅበላ አቅም ከፍ ማድረጉ የሁሉም ባለሙያ ውጤት መሆኑ ጠቁመው ባለሙያውን አመስግነዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩ ጥሩ ስራዎችን በማስቀጠል ሁሉም ባለሙያ የግል ዕቅድ በማዘጋጀት እንደሁም ወራዊና ሳምንታዊ ዕቅድ በማውጣት ሁሉም የበኩሉን ከተወጣ ዕቅዱ እንደሚሳካ ተናግረዋል፡፡
በኢንስትቲዩቱ የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ አቶ ተመስገን ሞገሴ የዝግጅት ምዕራፉን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ከ2011 ዓ.ም ክንውን በመነሳት የታዩ ክፍተቶችን በመሙላትና የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በሁሉም ዘርፍ ሰፋፊ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡
አንዳድ ተሳታፊዎች የዘንድሮ የተማሪ ቅበላ አቅም መጨመሩ በትምህርት ጥራት ላይ ችግር አያመጣም ወይ የሚል የስጋት ጥያቄ በመነሳቱ በቤቱ ስፊ ውይይት ተደርጎ ምላሽ ተስጥቷል፡፡
በተጨማሪም የሆቴል ትምህርት ክፍል ተሳታፊዎች እንደሌላው ትኩረት እንዳልተስጠ በመግለጽ ለክፍሉ መምህራን ስልጠናን ተደራሽ ማድረግም እንደሚቀር እና አቅማቸውም በስልጠና ማጎልበት እንዳሚገባ እንደ ተናግረው ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ጋር የአስልጣኞች ስልጠና ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ከሚመለከታችው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ይህ የዝግጅት ምዕራፍ ዕቅድና አፈፃፀም ግምገማ ከሰኞ ጀምሮ በዘርፍና በማኔጅመንት ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ዛሬ አርብ መስከረም 30/2012 ዓ.ም ከሰራተኛው ጋር የተደረገ የውይይት ማጠቃለያ ነው፡፡