ከአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ከ70 የሚበልጡ ሉዑካን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ለኢንቨስትመንትና ለትምህርት ከመጡ ልዑካን ቡድንን አባላት የካርሎስ ሮዛሪዮ ኢንተርናሽናል ፐብሊክ ቻርተር ትምህርት ቤት አንዱ ሲሆን ከዚህ ትምህርትቤት ጋር በርካታ ግንኙነቶችን ለማድረግ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አሊሰን ኮኮሮስ እና በዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ባውዘር እንዲሁም በዋና ዳይሬክተራችን ወ/ሮ አስቴር ዳዊትና በከተማችን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ አስቴር ካርሎስ ሮዛሪዮና ሆ/ቱ/ስ/ማ/ኢ ላለፉት 50ዓመታት ስልጠና በመስጠት ረጅም ዓመታትን ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህ ከሁለቱ እህትማማች ከተሞች ጋር ያለውን ልምድ በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚረዳቸው ገልፀዋል፡፡
ይህ የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረምና የዝግጅቱ አካል እንዲሆን ያስተባበሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋንና የልዑካን ቡድኑን አመስግነዋል፡፡ የካርሎስ ሮዛሪዮ ፐብልክ ስኩል ዳይሬክተር ሚስ አሊሰን ከሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ጋር የተደረገው ስምምነት የሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪውን ለማሳደግ የሚረዳ እና በርካታ ልምድ ሚቀሰምበት እንደሆነ ገልፀው በተቋማቸው ካሉ 2000 ተማሪዎች 400ዎቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውና እዚህ መጥተው ባዩት ነገር በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ባውዘር በበኩላቸው ይህ አጋጣሚ የነዚህን ሁለት እህትማማች ተቋማት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልፀው የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ የሚያስፈልገውን እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
በመጨረሻም ለክብርት ከንቲባዋና ለካርሎስ ሮዛሪዮ ስኩል ዳይሬክተር ከተቋማችን የማስታወሻ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
Recent Comments