የካቲት 27/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በዕለቱ በክብር እንግድነት በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው በዚህ አስቸጋሪ በኮቪድ ወቅታ የነበሩትን በማለፍ ለምርቃት በመብቊታችሁ ተማሪዎችን እና የተቋሙ ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ዘንድሮ የተመረቃችሁ ተመራቂዎች በቱሪዝም መሆኑ እጥፍ ድርብ ያደርገዎል ብለው በዚህም ከባለሙያነት ባለፈ የሀገር አምባሳደሮች በመሆናችሁ በሃላፊነት መስራት አለባችሁ ብለው ቱሪዝም ለሀገር ኢኮኖሚ ያለውን ፋይዳ ተግባራዊ ለማድረግ ከተመራቂዎች ብዙ ስለሚጠበቅ በትጋት መስራት እንዳለባችው ተናግረዋል።
የትምህርት ጥራትና አገልግሎት በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ከተመራቂ ተማሪዎች ይጠበቃል ያሉት ፕሮፌሰር አፍወርቅ ካሱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ መንግስት እና ህዝብ የሰጣችሁን ሀላፊነት በመወጣት ከዘርፉ የሚገኘውን ፍይዳ ሀገራችን እንድታገኝ የዜግነት ግዴታቸው እንዲወጡ ጥሪያቸው አስተላልፈዋል።
ከዘንድሮ ተመራቂዎቻችን ብዙ ቁጥር ያላቸው እና ከፍተኛ ውጤት ያመጡት ሴት ተማሪዎች በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው የተናገሩት የተቋሙ ዋና ዳይረክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በባለፈው ዓመት መመረቅ ሲገባችው በርካታ መሰናክሎችን አልፍችሁ ለዚህ መብቃታችሁ እንዳስደሰታቸው ተናግረው ይህ እንዲሆን ለተጉ የተቋሙ ሰራተኞችና የተመራቂ ተማሪዎች ወላጆችን ምስጋና አቅርበዋል።
በዘንድሮ መርሀ ግብርም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በድግሪ 16 ተመራቂዎች ፣በደረጃ 3 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 202 ተመራቂዎች፣ በደረጃ 4 በሆቴል እና ቱሪዝም 157 ተመራቂዎች እንዲሁም በደረጃ 5 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 53 ተመራቂ ተማሪዎችን። በአጠቃላይ 425 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በመርሀ ግብሩም ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።