ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ጥቅምት 02/2012
አንጋፋው ተቋም ራሱን በአዲስ የምዕራፍ ለማስጓዝ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ገልፀዋል ።

ተቋሙን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ቱሪዝም ዲፓርትመንት ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በጋራ ለመስራት መታቀዱን አቶ ገዛኸኝ ተናግረዋል ።

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከ50 ዓመታት በላይ በብቸኘነት የዘርፉን ባለሙያዎች ሲያፈራ የቆየ አንጋፋ ተቋም በመሆኑ የዕድሜውን ያህል አለማደጉ የሚያስቆጭ እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ ።

ዛሬ ለሚከፈቱ ዩኒቨርስቲዎች የልምድ መቀመሪያ መሆን የሚገባው ተቋም በዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛው መርሃግብር መስጠት አለመቻሉ ኢንስቲትዩቱ ምን ያህል መዘንጋቱን ማሳያ ነው ።

ኢንስቲትዩቱ ስልጠናውን የሚሰጠው በገነት ሆቴል ነው። ይህ ሆቴል ዛሬ የሰው ሀይል ከሚፈልጉት ሆቴሎች ደረጃ ጋር የሚቀራረብ ባለመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ ማስተማሪያ ሆቴል ሊኖረውና ብቃት ያለቸው ባለሙያዎች ሊያፈራ ይገባል ።

አሁን አንድ ተስፋ ይታያል ። የኢንስቲትዩቱ አመራሮች ቁጭት አድሮባቸው ለውጥ ለማምጣት ፍላጎቱ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ያላቸው ናቸው ። የሚያግዛቸው ህጎች በወቅቱ ፀድቀው ወደ ተግባር ሊገቡላቸው ይገባል ።

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ የ2012 በጀት ዓመት የ3 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል ።