ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሊድዋይስ ድርጅት ጋር በመሆን ዘመኑ የደረሰበትን የሆቴል አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀብት ተሰጥኦ ማስተዳደር ላይ ለሆቴል ሥራ አስኪያጆችና ሰው ሀብት ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።የስልጠና መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ማሰልጠኛ ተቋሙ በዘርፉ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሰለጠነ የሰው ሀይል እያቀረበ ነው፣ በዘርፉ ላይ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችንም እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በልዩ ሁኔታ ትኩረት የሚፈልጉ መሰል ጉዳዮች ላይም በዚህ ዘርፍ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የሊድዋይስ ሥራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ መኮንን በበኩላቸው የላቀ አገልግሎት ለመስጠት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ መስራት ፣ተገቢ የሥራ አካባቢ መፍጠር እና ሁል ጊዜ የመማር ስርዓትን መዘርጋት ነው ብለዋል።
የሆቴል መሪዎች ደምበኞች ከጠበቁት በላይ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መንገድ የሰው ሃብት ላይ መስራት ፣ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ይገባል ያሉት አቶ መልካሙ ይህን ለማሳካት ቀጣይነት ያለው ለውጥ ውስጥ መምራት እንደሚገባ ተናግሯል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎች ዘመናችን የደረሰበትን አገልግሎት በመስጠት ተወዳዳሪ ለመሆን የደምበኞች ፍላጎት የተከተለ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በሀገራችን የሚገኙ ሆቴሎች በራሳቸው ፖሊሲና መስጠት የሚፈልጉትን አይነት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ መኖራቸውን ያነሱት ተሳታፊዎቹ ዓለም ከደረሰበት አገልግሎት አንጻር ተወዳዳሪ ለመሆን ባላቸው ሰው ሀብት ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments