የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሆቴል ዲፓርትመንት ሰልጣኞች በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችንና ሎጆች ላይ ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል።

ፓራዳይዝ ሎጅ በአርባምንጭ ከሚገኙ ትልቁ ሎጅ ሲሆን ከሌላው ለየት የሚያደርገው በሪስቶራንት እንግዶች ሲቀመጡ የሚታዩ አባያና ጫሞ ሀይቆች ሁለቱ እንዳይገናኙ የተፈጠረ የእግዚር ድልድይ ነው። ሎጁን ያስጎበኘችው የሎጅ እንግዳ ተቀባይ ቤዛዊት ሳልኬ ከመግቢያው ጀምሮ የሎጅ ወሳኝ የተባሉ ክፍሎችን ለሰልጣኞች አስጎብኝታለች።
ሌላው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ እና የአዞ እርባታም ተጎብኝቷል።