ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ግንቦት 07/2011 ዓ.ምየሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዮ በዓል ዝግጅትን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫና የማነቃቀያ መርሐግብር ተደረገ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ የበዓል ዝግጅቱ ዓላማ ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ሰራተኞችና አጠቃላይ የተቋሙ ማህበረሰብ ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ በመስራት ለኢንስቲትዩቱ ቀጣይ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል፡፡
የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱን ሀምሳ ዓመት ጉዞን አስመልክቶ በስልጠና ዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የቀጣይ ስራ አቅጣጫ ግብዓት ማሰባሰብ ነው፡፡
የ50ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዮ በዓል ዋና ዋና መርሐግብሮች ለይ ማበራሪያ የሰጡት የሁነቱ ምክትል ሰብሳቢ መምህር ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት በዓሉ ከሰኔ 01-03 /2011 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን በዘርፉ ምሁራን የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት ታላቅ ጉባኤ የተዘጋጀበት፣ ቀጣሪ ድርጅቶችና ስራ ፈላጊዎች የሚገናኙበት (job fair), ኤግዝቢሽን፣ የተለያዩ መዝናኛዎች እና ሌሎችም ዝግጅቶች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
Recent Comments