ሚያዝያ 2/2015 ዓ. ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከክልል ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ የቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች እንዲሁም ከሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ምክክር አደረጉ
በምክክር መድረኩ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት በዚህ ዘመን የሙያና ክህሎት ስልጠና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት የሳበ ከመሆኑ ባለፈ ለሰው ልጆች ለኢኮኖሚ ችግር መፍትሔ ሰጪ ሆኖ ሲወሰድ እናያለን ብለዋል።
ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሀገራዊ ብልጽግናን ለማሳካት፣ በሙያው የላቀ ክህሎትና ብቃት ያለው የሰው ሀይል ማፍራት ከሁሉም የተሰወረ አይደለም። ከዚህም የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳካት በዘላቂነት በመስራት ኢትዮጵያን በዓለም ደረጃ ከፍ ያደርጋሉ ከተባሉት አምስቱ የልማት ቁልፍ ዘርፎች አንዱ ቱሪዝም መሆኑ ይታወቃል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተልዕኮ በዘርፉ የላቀ ስልጠና፣ የላቀ ጥናትና ምርምርና ማማከር አገልግሎት መስጠት ነው። ከዚህም ባለፈ ጥናት ላይ የተመሰረተ የገበያ ፍላጎት የሚያሟሉ ስልጠናዎችን ይሰጣል። ስለሆነም ኢንስቲትዩቱ መንግስት የሰጠውን ተልዕኮ ብቻውን ሳይሆን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ መስራት እንደሚያስፈልገው በማመን ይህ የምክክር መድረክ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል።
መንግስት ሁሉም የስልጠና ማዕከላት ተልዕኮው ከማሰልጠን በላይ ነው የሚለውን ሀሳብ በመያዝ በጥናትና ምርምር በማማከር እና በማህበረሰብ አቀፍ ሥራዎች በጋራ መስራት ዜጎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሙያዊ ብቃት ያለው ዜጋ ለማፍራት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ጥሩ የምክክር ጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።
Recent Comments