ቱ ማ ኢ ታህሳስ 4/2018 ዓ ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀጥታ ከደንበኛ አገልግሎት ጋር የሚገናኙ የሥራ ክፍሎችን መሰረት ያደረገ የላቀ ደንበኛ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው። የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በስልጠና መክፈቻ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ከደንበኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችን የላቀ ደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖራቸው የሚያስችል ስልጠና በኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች በመስጠት
ጅማሮውን እንዳደረገ ገልጸው ተቋማችን ደንበኛን በመቀበል ምስጉን እንዲሆኑ እንዲሁም አሰልጣኞቻችን ከተቋም አልፎ በሌሎች ተቋማት ያለውን የደንበኛ አያያዝ ችግር በስልጠና መቅረፍ የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ማሳየት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የተቋሙ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለፁት ይህ ስልጠና በተቋማችን የላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ለመጨመር በስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ታቅዶ ውጤቱም በየጊዜው የሚለካ በመሆኑ ተሳታፊዎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ።
የዛሬው ስልጠና በሁለት ርዕሶች በተቋማችን አሰልጣኞች አቶ ዳንኤል በቀለ እና አቶ መለሰ ወርቁ የተሰጠ ሲሆን በአቶ ዳንኤል በቀለ የላቀ ደንበኛ አገልግሎት የምንሰጠው ለማነው የሚልና በተቋማችን የላቀ የደንበኛ አገልግሎት ባህል ለማድረግ ምን ያስፈልጋል የሚሉትን ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ሌላው በአሰልጣኝ መለሰ ወርቁ በደንበኛ አያያዝ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከራስ አልፎ እንደሀገር የሚታየውን የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመፍታት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።
ስልጠናው ለቀጣይ ሦስት ቀናት በተለያዩ ርዕሶችና አሰልጣኞች የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments