ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ጥር 18 /2013 ዓ.ም
ለሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ሰራተኞች በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የቀጣይ አስር ዓመታት ለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የተዘጋጀው በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ፍኖተ ካርታ እውቀትና ክህሎት ላይ የተመሰረተ የመንግስት አስተዳደር ዘርፍ የሚያመጣ ነው ብለዋል፡፡
የለውጥ ፕሮግራሞቹ ነጻ፣ገለልተኛና ብቃት ያለው አገልጋይ መፍጠር፣ የሰው ሀብት ልማት አስተዳደርና የብቃት ማረጋገጫ፣ የእሴት ግምባታና ስነ ምግባር እና ውጤታማ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ስልጠናውን የሰጡት የተቃቋመሙ ባለ ሙያዎች አቶ ሰለሞን አሰፋ እና አቶ ታምራት ተፈራ ገልጸዋል፡፡
ከተሳታፊዎችም ግብዓት የሚሆኑ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
Recent Comments