ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ዕንግዳ ተቀባይነት ሳምንት (National Annual Tourism and Hospitality week) ለ8ኛ ጊዜ ከግንቦት 15 እስከ 17/2013 ዓ.ም. “ቱሪዝም ለሰላም፤ ሰላም ለቱሪዝም!” በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለድርሻ አካላት እና የተቋሙ ማህበረሰብ በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለማክበር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ይህን ሃገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት የፕሮግራም መክፈቻ መርሐግብር በሚከናወንበት እሁድ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም ከጧቱ 1፡30 በመገኘት የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡልን የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
አድራሻ፡ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ገነት ሆቴል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ፡-0115308121 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡