መስከረም 5/2016 ዓ ም
ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ተቋሙ ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱ

የማማከር እና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በመስጠት ማህበረሰቡን መደገፍ መሆኑን ጠቁመው ፤ ዘንድሮ ከተያዙ ዕቅዶች ለመጀመሪያ ዙር በበሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 71 ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ስምንት ከተሞች መመረጣቸውን ገልጸዋል፡፡
የማማከር አገልግሎቱ ዓላማ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ወደ የከተሞቹ ሆቴሎችና የቱሪስት መዳረሻዎች መንቀሳቀሳቸው ስለማይቀር ሙያዊና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ፣ የውስጥ አደረጃጀታቸውን እንዲያሻሽሉ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡
በአገልግሎቱ ሆቴሎች ባለ ኮኮብእና ወደ ኮኮብ ሆቴልነት እያደጉ ያሉት ተካተዋል። የዶሽ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አለሙ እንደተናገሩት ይህ አይነት የማማከር አገልግሎት ሰፊ ጊዜ ተወስዶ የሚሰጥ ቢሆን የተሻለ እንደሆነና አጭር ሰዓት ቢሆንም ጥሩ ልምድ እንዳገኙ ተናግረዋል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።