ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ መጋቢት 09/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከልና የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ አብሮ ለመስራት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊትና የአካዳሚው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተወያይቷል፡፡
ተቋማቱ አብሮ ለመስራት የጋራ ስምምነት የነበራቸው ሲሆን በአፈጻጸሙ ዙሪያ እና በቀጣይም ስምምነት ሰነዱን በማሻሻል በትምህርትና ስልጠና ፣ በቴክኖጂ ሽግግርና ሌሎችም ዘርፎች አብሮ በመስራት የሀገራችንን የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል፡፡