ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰራተኞች ከተቋሙ ቦርድ አመራሮች ጋር ትውውቅና ስትራቴጅካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት የተቋሙ መዋቅር ማሻሸያ፣ ሊኖረው ስለሚገቡ የአሰራር ስርዓት ማሻሸያዎችና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዕቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የማሰልጠኛ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣና ወቅቱን የሚመጥን አገልገሎት መስጠት እንዲችል ከሰራተኞች፣ አመራሮች፣ ቦርድ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል የተቋሙን የኖረ ስምና ዝና ማስቀጠል እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።
የማሰልጠኛ ማዕከሉ የቦርድ አባላት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሆቴል ባለሙያዎች ማህበር፣ ከሆቴልና መሰል ሙያዎች አሰሪዎች ፌዴሬሽን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርቶች ማህበር፣ ከአዲስአበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር፣ ከፌዴራል ቴክኒካል ዩኒቨርስቲና ሌሎች አደረጃጀት የተውጣጡ ጠንካራ አቅም ያለው ነው ።