ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሰኔ 10/2013 ዓ.ም
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የመለመላቸውን ከ350 በላይ የአንደኛ ዓመት ሰልጣኞችን አቀባበል አደረገ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ሁሉን አቀፍ ወደ ሆነው የቱሪዝም ዘርፍ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡ አዳዲስ ሰልጣኞች ወደ ዘርፉ እየተቀላቀሉ መምጣታቸው ለሀገራችን የቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የአካዳሚክና ምርምር ዲን አቶ አብርሃም ለገሰ በበኩላቸው የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ የስራ እድል የሚገኝበት በመሆኑ ሰልጣኞች ጠንከረው በመማር ስኬታማ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የአስተዳደርና ልማት ዲኑ አቶ ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ተቋሙ በቂ የተግባር ስልጠና ቤተሙከራዎችና ግብዓቶች መኖሩን ገልጸው በቀጣይም የተሻለ አቅርቦትና ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች እንዲኖሩ እንሰራለን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተቋሙ የሰልጣኞች ስነምግባር ደምብ፣የኮቪድ 19 ፕሮቶኮልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቶች ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም የማዕከሉ የቀድሞ ሰልጣኞች የነበራቸውን ልምድ ለአዲስ ሰልጣኞች አካፍሏል፡፡