ሚያዚያ 6/2013 ዓ.ም ሆ.ቱሥ.ማ.ማ የማሰልጠኛ ማዕከሉ የበላይ አመራሮች፣ ሠራተኞችና መምህራን በመማር ማስተማር ዙሪያ ከሰልጣኞች የቀረቡ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ጭምር በማካተት ቀጣይ ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
በተቋሙ የተገልጋይ እርካታን በተመለከተ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገው ጥናት ውጤቱ የተገልጋዩ እርካታ እየቀነሰ መምጣቱን የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ አስረድተዋል፡፡
በዚህም መነሻ ሁሉም መምህራንና ሰራተኞች የታየባቸውን የስራ ላይ ክፍተት በመቅረፍ ቀጣይ ሃላፊነታቸውን የማይወጡ ኃላፊዎችና ሰራተኞችን በትኩረት እንዲከታተሉ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
የበላይ አመራሩም የቀረበው ሃሳብ ከመካከለኛ አመራሩ ጋር ውይይት በማድረግ ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ሥርዓትን በመተግበር ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተካከል ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡