ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ከመላው ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ማዕከሉ በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግት የታቀዱ ስራዎች በተሻለ ሁኔታ መፈጸማቸውን ገልጸው በተለይ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሀገራችን የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ ሀገራዊ ጥናት መካሄዱ፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች መከናወናቸው፣ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች በስፋት መሰጠታቸው የአሰራር ስርዓቶች ለማስተካከል የተለያዩ መመሪያዎች መዘጋጀታቸውና ተቋማዊ መዋቅርን ለማስተካከል የተከናወኑ ስራዎች በጠንካራ ጎን የሚታዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በበኩላቸው የማሰልጠኛ ማዕከሉ አፈጻጸም ጥሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አቅጣጫ ሰጥቷል።
ሰራተኞችም በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት አክሏል።