ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ የካቲት 21/2012
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የሰራተኞች መብትና ግዴታን አስመልክቶ በነበሩት የመንግስት ሰራተኞች አዋጅና ደምቦች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የማዕከሉ ምክትል ዋና ዳይሬከተር አቶ ገዛኸኝ አባተ የሰራተኞች ህግ ማዕቀፎች ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፣ ሰራተኞች መብትና ግዴታቸውን አውቀው በቅንነት ማገልገል አለባቸው ብለዋል፡፡
ስልጠናው በሰራተኞች መብትና ግዴታዎች ዙሪያ እንተቋም የሚታዩ የህግ አተገባበር ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ አቶ ገዛኸኝ አባተ ገልጸዋል፡፡
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከልም መምህር ታረቀኝ መኮንን ስልጠናው በሰራተኞች ደምብና መመሪያዎች ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡