የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ በሸገር ከተማ አስተዳደር መነ አብቹ ክ/ከተማ ሁለተኛ ዙር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ።ቱ.ማ.ኢ ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ቱሪዝምና አረንጓዴ አሻራ የሚለያዩ አይደለም፣ መነ አብቹ ክፍለ ከተማ ተገኝተን ዛሬ ብቻ ችግኝ ተክለን የምንሄድ ሳይሆን በቀጣይ ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው የስልጠና እና ምርምር ስራዎች በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የመነ አብቹ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ብርሃኑ ኢንስቲትዩቱ በሰሜን በር መውጫ በሆነው አካባቢ ችግኝ ለመትከል ስለመረጠ እናመሰግናለን ፣ ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ እና በሌሎችም ጉዳዮች አብረን እንሰራለን ብለዋል።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት ሁለተኛ ዙር በመነ አብቹ ክ/ከተማ ሱሉልታ አካባቢ ኢፋ ቦሩ መልካ ሀዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተተከሉት ችግኞች 1500 ሲሆኑ ለምግብነት፣ ለደንና ውበት የሚያገለግሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ቱሪዝምና አረንጓዴ አሻራ የሚለያዩ አይደለም፣ መነ አብቹ ክፍለ ከተማ ተገኝተን ዛሬ ብቻ ችግኝ ተክለን የምንሄድ ሳይሆን በቀጣይ ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው የስልጠና እና ምርምር ስራዎች በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የመነ አብቹ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ብርሃኑ ኢንስቲትዩቱ በሰሜን በር መውጫ በሆነው አካባቢ ችግኝ ለመትከል ስለመረጠ እናመሰግናለን ፣ ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ እና በሌሎችም ጉዳዮች አብረን እንሰራለን ብለዋል።
ትክክለኛ የተቋሙን መረጃዎች ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/