ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በቦሌ ለሚ እንዱስትሪ ፓርክ ችግኝ ተከሉ።
ቱ.ማ.ኢ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም

“የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ ” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በቦሌ ለሚ እንዱስትሪ ፓርክ ችግኝ ተከሉ።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ነገ ለልጆቻችን የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ፣ ለዜጎች የሥራ እድልንም ለመፍጠር የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት ተቋሙ በጥያ ትክል ድንጋይ፣ ፖርቹጋል ድልድይ እና ሌሎችም ቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች ላይ የተተከሉ 80 በመቶ ችግኞች መጽደቃቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ከቢሮ ጋር የሀገራችንን ቱሪዝም ለማሳደግ ለአንድ ዓላማ አብረን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ ሀፍቶም ገ/ እግዚአብሔር በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በቱሪዝም ዘርፍ እያበረከተ ካለው አስተዋጽኦ በተጨማሪ በመዳረሻዎች አካባቢ እያደረገ ያለው የችግኝ ተከላ መርሐግብር የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸው ዛሬ አብረን የተከልነውን በጋራ ተንከባክበን እናለማለን ብለዋል።
በዚህ መርሐ ግብር 2000 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ በክረምት እየሰለጠኑ ያሉ የሸጋ ትውልድ ህፃናትም ተሳትፈዋል።
ትክክለኛ የተቋሙን መረጃዎች ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/