የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተገመገመ
የተጠሪ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተገምግሟል።
በመድረኩ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት፣ የቱሪዝም ኢንስቲቲዩት እና የኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የአምስቱ የግብርና ኮሌጆች ዕቅድ አፈፃፀም በየተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋማቱ የተሻለ አፈፃፀሞችን አልቆ ማፅናት እና ክፍተቶችን በፍጥነት ማረምና መሙላት እንደሚገባ አሳስበው ይህንንም በልዩ ዕቅድ ለመመለስና ሪፎርሙን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ህዳር 21፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/…/ministry-of-labor-skill-fdre
Recent Comments