የካቲት 14/2014 ዓ ም ሰልጣኞቻችን በአርባምንጭ ቆይታቸው ስለከተማዋ በቂ መረጃ እያሰባሰቡ ይገኛሉ። አርባምንጭ ሁለት ከተሞች አሉዋት። አንደኛው ስቀላ ሲሆን ሌላኛው ሽቻ ነው።
ስቀላ የንግድ ማዕከል በመሆን ሲታወቅ ሽቻ የመንግስት ተቋማት ይገኙበታል።
በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙት ሀይቆች አባያና ጫሞ ይባላሉ ። የሀይቆቹ አፈጣጠር በድሮ ዘመን ለሦስት ዓመት ሳይቋረጥ በዘነበው ዝናብ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል።
ጫሞ ማለት ትርጉም ምሬት ማለት ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ከጦርነት ሽሽት ሰዎች በህይወት እያሉ እየገቡ የሞቱበት በመሆኑ ስያሜውን አግኝቷል።
ሌላው አርባምንጭ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በ1967 ዓ ም ተመሰረተ ነው፤ 514 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሲኖረው ከ91 በላይ አጥቢ እንስሳት ፣ 350 ያህል አእዋፋት፣ ከ900 እስከ 1000 እፀዋት የሚገኙበት እንደሆነ የፓርኩ አስጎብኝ አቶ ንጉሴ ደምጦ ተናግረዋል።
በዚህ ፓርክ 40 ምንጮች ፣ የእግዜር ድልድይ ፣ አዞ ገበያ ፣ ፍል ውሃ ልዩ የተፈጥሮ መስህብ ናቸው።
የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሜዳ አህያ የሚገኝበት እንደሆነም ተገልጿል።
Recent Comments