ቱ.ማ.ኢ ጥር 18/2016 የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የግማሽ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሰራተኞች ቀረበ።…
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተሰሩ ሥራዎችን ከስር ከስሩ እየገመገምን የመጣን ቢሆንም አሁን ላይ ቀሪውን የስድስት ወር አፈፃፀም የተሻለ ለማድረግ ያለፈውን መገምገም ብቻ ሳይሆን የመረጃ ልውውጥ በማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን የዕቅድ ክፍል ተ/ ዳይሬክተር አቶ ተመሰገን በቀለ እና የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ክንውን በአቶ ሰለሞን አሰፋ የለውጥና መልካም አስተዳደር ተ/ዳይሬክተር ቀርቧል።
በሪፖርቱ ከዚህ በፊት በሰራተኛው ቅሬታ ቀርቦባቸው መልስ ያገኙ፣ እየተሰሩ ያሉ እና ያልተፈቱ ያሏቸውን እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች አንስተዋል። በቀረበው ሪፖርት ከሰራተኛው አስተያየትና ጥያቄ ቀርቧል።
በከሰዓት ፕሮግራም የሥራ ላይ ጤንነት እና ጤናማ የሥራ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል አካላዊ ፣ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስልጠና በዶ/ር ሰላም አክሊሉ የዌልነስና ካሮፕራክቲክ ክሊኒክ ባለቤት ተሰጥቷል። ዶ/ር ሰላም አክሊሉ አስር ለጤና፣ ከቤት እስከ መስሪያ ቤት በሚል ስልጠና በስጠት ይታወቃሉ ።
Recent Comments