ሰልጣኞችን በማስተባበር የበጎ አድራጎት ሥራዎች ለማከናወን ፕሮግራም መያዛቸውን የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ተማሪ ዓለም ፀሀይ ጥጋቡ ተናገረች፡፡

ሰልጣኞችን በማስተባበር አሁን ካለው ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር የበጎ አድራጎት ክበብ መጠናከር እንዳለበትና በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊታችን ድጋፍ እንደሚያሰባስቡ ተናግራ ለዚህ በጎ አድራጎት ሥራ የተቋሙ ማህበረሰብ ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ስለሆነም ሀሙስ ህዳር 16/2014 ዓ.ም በገነት ሆቴልና በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ትብብር የተቋሙ ሰልጣኞች በዋናነት መምህራንና ሠራተኞች የሚሳተፉበት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
• የበጎ አድራጎት ሥራዎች፤
• የጽዳት ዘመቻ፤
• የደም ልገሳ ፤
• የደረቅ ምግብ ዝግጅት፤
• የአልባሳትና ቁሳቁስ ማሰባሰብ ዝግጅቶች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
ድል ለመከላከያ ሰራዊታችን!!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች