ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ የካቲት 19/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማስልጠኛ ማዕከል የህግ ክፍል ለተቋሙ ሊረዱ የሚችሉ የተለያዩ መመሪያዎችን እያዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በተቋሙ እንደ መልካም አስተዳደር ችግር እየታዩ የመጡ ጉዳዮችን ሊፈታ የሚችል መመሪያ እያዘጋጁ እንደሆነ አቶ ግርማ ገመቹ ተናገሩ፡፡ የህግ ክፍሉን ጨምሮ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ 13 አባላት ያሉት ቡድን በማዋቀር ራሳቸውን በሶስት ዝቅተኛ ቡድን በማከፋፈል በተለያዪ ዘርፎች ማለትም በሬጅስትራር፣ የማታና አጫጭር፣ ምርምር ክፍሎችንና የስነምግባር መመሪያዎችን እያዘጋጁ እንደሆነ የህግ ክፍሉ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ያለበትን ደረጃና ሂደቱን ለመከታተል በቦታው የተገኙት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደተናገሩት ቡድኑ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑንና ተቋሙ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮችም መፍትሔ የሚሆኑ መመሪያዎች ሊዘጋጁ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ ይዞ የሚመጣውም መመሪያ በተለያዩ አካላት በመታየት ወደስራ እስከሚገባ ድረስ ተስፋ ሳይቆረጥ በጥንካሬ መሰራት እንዳለበት አቶ ገዛኸኝ አሳስበዋል፡፡