መጋቢት 24/2013 ዓ.ም ሆ.ቱሥ.ማ.ማ የማሰልጠኛ ማዕከሉ የበላይ አመራሮችና የተማሪ ተወካዮች በመማር ማስተማር ዙሪያ በጥንካሬና በድክመት የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ::
በውይይቱ ሁሉም የተቋሙ የበላይ አመራር በተገኙበት የተማሪ ተወካዮች በተቋሙ የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎን በማንሳት በቀጣይ ለመማር ማስተማር ሂደት ይረዳን ዘንድ በነጻነት እንዲ ያቀርቡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በማሳሰብ ወይይቱን አስጀምረዋል፡፡
በማሳሰቢያው መሰረት የተማሪ ተወካዮች በተቋሙ የሚታዩ ጠንካራ ጎኖች የበላይ አመራር አካላት የተማሪውን ጥያቄዎች ወደታች እየወረዳችሁ በማየት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ጥሩ እንደሆነና በተቋሙ የሚሰጡ ትምህርቶችን በተክኖሎጂ መጠቀሙ የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ተወካዮቹ በድክመት ያነሷቸው በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተዘጋጅተው የሚያስተምሩ መምህራን እንዳሉ ሁሉ ያለዝግጀት መግባትና የሚቀሩ እንዳሉ ይህንንም የበላ አመራሩ ቁጥጥር እንዲያደርጉበት ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ተወካዮቹ ለቀጣይ የሚጠቅሙን ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚገቡ ናቸው ያሏቸውን ለቋንቋ ትምህርት ቱኩረት ቢሰጥ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ግቢ ውስጥ ሙሉ ቢሆን፣ ቤተመጸሐፍት ቅዳሜና እሁድ ቢሰራ፣ የመማሪያ ክፍል አደረጃጀቶች ችግር ቢፈታ፣ የውጤት አሰጣጥ ከሬጅስትራር ጋር የተያያዙ ችግሮች መፍትሔ ቢያገኙ፣ የግቢ ጽዳትና የውሃ ችግር ቢስተካከል እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎች ቢበረታቱ የሚሉ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡
በሌላም የኪስ ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ለብዙ ችግር መጋለጣቸውንና ለኮቪድ መከላከያ የሚሰጡ እንደማክስና ሳንታይዘር ያሉት በጊዜ ቢቀርብልን በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ አካዳሚክና ምርምር ዲን አቶ አብርሃም ለገሰ እና የአስተዳደር ልማት ዲን አቶ ዳንኤል በቀለ ከተማሪዎች በዘርፋቸው ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ተማሪ ተወካዮቹ በጠናካራና በደካማ ጎን የቀረበውን ሀሳብ አመስግነው፤ በተቋም ደረጃ ሊስተካከሉ የሚችሉ የኮቪድ ፕሮቶኮል እቃዎች በቶሎ እንዲደርስ ለማድረግና በቅጥር ግቢ ውስጥ የኢንተርኔት አክሰስ ሙሉ እንዲሆን እንዲሁም የዓመታዊ ሁነት ስራው ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተቀናጅቶ ዘመናዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ የተማሪዎች የኪስ ገንዘብ በተቋም ደረጃ ማስተካከል ባይቻልም የማደሪያ ጉዳይ ቀጣይ እቅዳችን አድርገን እንሰራለን በማለት ውይይቱን አጠናቀዋል፡፡