ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ነሐሴ 10/2011 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሆቴሎች የአካል ምልከታ ለማድረግና ግብዓት ለማሰባሰብ የመስክ ጉብኝት ሊያደርግ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ኢንስቲትዩቱ ላለፉት 50 ዓመታት የሆስፒታሊቲ ኢንዱሰትሪን መደገፍ የሚችል በስኩ የሰለጠነ የሰው ኃይል ሲያቀርብ የቆየ አንጋፋ ተቋም ሲሆን የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና ከሆቴሎችና ከቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ግብዓት ማሰባሰብ በዚህ የዝግጅት ምዕራፍ የታቀዱ ሥራዎች እንደሆኑ የጉዞው አስተባባሪና የቱሪዝም ትምህርት ክፍል አቶ ኪዳነ ገረሱ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ጉዞው የተቋማችንን ማህበረሰብ በማሳተፍ ክፍተቶችን ከመነሻቸው በመለየት በቀጣይ የስራ ዘመን ለሚሰሩ ስራዎች ለእቅድ ዝግጅት ግብአት ማሰባሰብ፣ የተቋሙን ዓላማና ራእይ ለማሳካት ከክልሎች በተለይ ከደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ የነበረንን ትስስር በአካል በመገምገም በነበሩን የጋራ ስራዎች ላይ ያስመዘገብናቸውን ጠንካራ ተግባራት እና ውስንነቶቻችንን በመለየት በቀጣይ በአካባቢው የሥልጠና ትኩረትና የሰው ኃይል መሙላት እንደሚገባ ቅድመ ዳሰሳ ለመንደፍያስችላል፡፡
በሌላም በኩል ይህን መሰል ጉዞ መዘጋጀቱ የተቋሙ ማህበረሰብ ከተሰማራበት ስራ አንፃር ከመዳረሻዎቹ (ከባለ ድርሻ አካላት) ጋር በመወያየት ለተቋማችን ስኬት ገንቢ ሀሳቦችን በመውሰድ የቀጣይ ትግበራዎችን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ስኬታማና የተሳለጠ የስራ እቅድ-ክንውን እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑን አቶ ኪዳኔ ይገልፃሉ፡፡
ጉዞው ከአዲስ አበባ፣ አሰላ ፣ ባሌ ሮቤ ፣መታሃራ ፣ ሀረር ፣ድሬደዋ ፣አዳማ ሲሆን በየከተሞቹ የሚገኙ ሆቴሎችና የቱሪዝም መዳረሻዎች ይጎበኛሉ፡፡
የጉዞው መነሻም ቅዳሜ ነሐሴ 18 እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
Recent Comments