መጋቢት 1/2017 ዓም.ቱ.ማ.ኢአዲስ ተገንብቶ በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከልን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች ዛሬ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም እንደተገለፀልን በአንድ ጊዜ አስር ሺህ ሰው ማስተናገድ የሚችል ትልቅ አዳራሽ እንዲሁም መለስተኛ የስብሰባ አዳራሾች ፣ አንድ ሺህ አልጋ ያላቸው ሁለት ሆቴሎች፣ ከሁለት ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ ፣የሥዕል አዳራሾች፣ ሪስቶራንቶች፣ አፊ ቲያትር የመሳሰሉ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን፣ ዓውደ ርዕይ ማስተናገድ የሚችል መሆኑን አስጎብኛችን አቶ ተመስገን ገልጸውልናል።በጉብኝቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት በሌሎች ሀገራት እያየን በኛ ሀገር እስከ ዛሬ አለመኖሩ ሲቀጨኝ ነበር አሁን በዚህ ደረጃ ተሰርቶ በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ብለዋል። የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በስልጠና በሚያስፈልገው ሁሉ ባለሙያዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።
አስጎብኛችን አቶ ተመስገን የኢንስቲትዩቱ የቀድሞ ሰልጣኝ እንደነበሩ ገልፀው በቱሪዝም ኢንደስትሪው የኢንስቲትዩቱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments