ቱ .ማ .ኢ ጥር 9/2015 ዓ ም በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የተቋሙ የበላይ ሀላፊዎች፣ የማናጅመንት አባላት እና የተቋሙ የስልጠና ጥራት ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ጉብኝት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ እንደገለጹት ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከተቋማቸው ጋር አብሮ ለመስራት አቅዶ መምጣቱን አመስግነው ፤ ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ብቸኛ ደረጃዎችን የሚያዘጋጅ ተቋም መሆኑን በመጠቆም ደረጃውን ማስተዋወቅና ስልጠና መስጠት ስራቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ አሁን ያለበትን የቢሮ አደረጃጀት ጉብኝት ተደርጓል። ጉብኝቱን የመሩት የተቋሙ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይስማቸው ደጉ እና የደረጃ ትግበራ ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ተፈራ ሲሆኑ እኛም እናንተን ለማብቃት እንሰራለን በማለት ከየትኛውም ደረጃና መዋቅር በመነሳት /ARSO/ ደረጃዎች ምደባ ላይ መድረስ እንደሚቻል ተናግረዋል።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ተቋሙ ረዥም እድሜ ያለው ቢሆንም አስፈላጊውን ርቀት አልሄደም ፤ ምክንያቱ ደግሞ የራሱ ስታንዳርድ ባለመኖሩ ነው ፤ አሁን ግን ካለበት ደረጃ በመነሳት ለቴክኒካል ኮሚቴዎችና ለአመራሩ ስልጠናዎች በመስጠትና ወርዶ በመደገፍ ለዚህ ለደረጃ እንደምንደርስ የሚያሳምን ተግባራትን ማየታቸውን ገልፀዋል።
ኢንስቲትዩቱ በአገሪቱ ካሉ የቴክኒክና የሙያ ተቋማት ከአሰሩ አንዱ በመሆን ISO-9001፡2015 ሰርተፊኬት እጩ ሆኖ መመረጡ ይታወሳል።