የካቲት 22/2014 ዓ ም በማጠቃለያውም አብያታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ አእዋፋት መካከል ሰጎኖችን ጎብኝተዋል። አብያታ ሻላ ፓርክ የሚታወቀው በአዕዋፋት እንደሆነም ተገልጿል።
በመጨረሻም ሰልጣኞችና መምህራን በዝዋይ ሀይቅ የጀልባ ጉዞ አድርገዋል።
በዚህ ትምህርታዊ ጉዞ ለሰልጣኞች በየሄድንበት ማረፊያ በመስጠት የተባበሩን የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ፣ አርባምንጭ ዩንቨርስቲ፣ ቱሪሚ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ ጂንካ ዩንቨርስቲ እና የሲዳማ ክልል አመራሮች ባህል ማዕከሉን በመፍቀድ ላደረጉት ትብብር እጀግ እናመሰግናለን።